=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ህሊናን ከሚያሳርፉ እና የጭንቀትና የሐሳብ ደመናን ከሚበታትኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ በተለያዩ ሀገራት መዟዟር ፣ ጋራ ሸንተረሮችን ማቇረጥ ፣ በሰፊዋ ምድር ላይ መሄድና ከተገለፀው የፍጥረተ-ዓለም መፅሐፍ ላይ እየተመለከቱ የአምላክነትን ብዕር በህዋው ገፆች ላይ ውብ አንቀፆችን ሲፅፉ ማየት ፣ ደስታን የሚፈጥሩ ድንቅ መናፈሻዎችን ፣ አፀዶችን እና የተጠላለፉ አትክልታማ ስፍራዎችን መቃኘት ነው።
ከቤትህ ውጣ፣ በዙሪያህ ያሉትን ተመልከት ፣ ከፊትና ከኋላህ ያሉትንም ቃኝ ፤ ተራራ ላይ ውጣ ፣ ሸለቆዎች ውስጥ ውረድ ፤ ዛፎች ላይም ውጣ ፣ ንፁህ ውሃ ተጎንጭ አፍንጫህን አበቦች ላይ አሳርፈህ በሚያውደው መዓዛቸው ነፍስህን አሳርፋት ፤ የዚያኔ ነፍስህን እንደዘማሪ ወፍ ነፃነት ተሰምቷት በደስታ ህዋ ላይ ስትንሳፈፍ ታገኛታለህ። ከቤትህ ውጣ ጥቁሩን ግርዶ ከዓይንህ አስወግድ ከዚያም አሏህ በፈጠራቸው ሰፋፊዎቹ ጎዳናዎች ላይ እያደስከውና እያጠራኸው ሂድ። ስራ ፈቶ ጠባብ ክፍል ውስጥ መሸጎጥ ራስን ለማጥፋት ቀላልና ውጤታማ መነገድ ነው። ዓለም ማለት ያቺ ትንሿ ክፍልህ አይደለችም። አንተም ሁሉም ሰዎች አይደለህም ታዲያ ለሃዘን ወታደሮች እጅህን መስጠት ለምን አስፈለገ። ንቃ! በዓይንህ በጆሮህና በልብህ ቀላሎችም ከባዶችም ኾናችሁ ተንቀሳቀሱ ብለህ ለልብ... በሃይቆች መካከልና የፍቅር ዲስኩሮችን በሚተርኩ ዘማሪ አዕዋፋት መካከል ሆነህ እንዲሁም ከኮረብታው ላይ ጀምሮ የነበረውን ጉዞውን በሚተርከው ወራጅ ውሃ መካከል ሆነህ ቁርአንን ለማንበብ ተነሳ።
ጭንቀት ለሚሰማቸው ሰዎችና ጠባቧ ክፍላቸው ለጨለመችባቸው ሰዎች ሃኪሞች የሚሠጡት ምክር በምድር ላይ እንዲንሸራሸሩ ነው። ታዲያ አሁኑኑ ተነሳ! አብሽር ተጔዝ። እንደሰት እናስተንትን ፣ እናስብ።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|